
ሰቆጣ: ሰኔ 13/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አሥተዳደር በአንደኛ ዙር በ179 ትምህርት ቤቶች የ6ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና እየተሰጠ መኾኑን የብሔረሰብ አሥተዳደሩ ትምህርት መምሪያ አስታውቋል። በብሔረሰብ አሥተዳደሩ 7ሺህ 590 ተማሪዎች ፈተናውን እየወሰዱ መኾኑን የትምህርት መምሪያ ኀላፊ ሰይፈ ሞገስ ገልጸዋል።
በአካባቢው ያለው አንጻራዊ ሰላም ፈተናውን በአግባቡ መፈተን እንዲቻል እገዛ ስለማድረጉ መምሪያ ኀላፊው አስገንዝበዋል፡፡ ተማሪዎች ተረጋግተው ዓመቱን ሙሉ የተዘጋጁበትን ትምህርት በውጤት ለማጠናቀቅ ከኩረጃ በመጽዳት ፈተናውን በአግባቡ እንዲሠሩ አሳስበዋል። ፈተናውም ከሰኔ 13/2016 ዓ.ም እስከ ሰኔ 14/2016 ዓ.ም ድረስ የሚሰጥ መኾኑን ከክልሉ ትምህርት ቢሮ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
ዘጋቢ፡- ደጀን ታምሩ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!