የክልሉን ሰላም ዘላቂ ለማድረግ ከመከላከያ ሠራዊት ጋር በጋራ መሥራት እንደሚገባ ተጠቆመ።

16

ደሴ: ሰኔ 12/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ላለፉት ሁለት ቀናት በወሎ ቀጣና ከሚገኙ ሁሉም ዞኖች የተውጣጡ ተወካይ ተጽዕኖ ፈጣሪ የኅብረተሰብ ክፍሎች የተሳተፉበት የሰላም ኮንፈረንስ ተካሂዷል። ”የጠነከረ ወንድማማችነትን መገንባት የፈተናዎች ሁሉ መሻገሪያ ድልድይ ነው” በሚል መሪ ሃሳብ በተካሄደው ኮንፈረንስ ለሰላም ቅድሚያ በመስጠት ሁሉም በትብብር ሊሠራ እንደሚገባ ተመላክቷል።

የክልሉን ሰላም ዘላቂ ለማድረግ ከመከላከያ ሠራዊት ጋር በጋራ መሠራት እንደሚገባም ተጠቅሷል። ኮንፍረንሱ ባለ አስር ነጥብ የአቋም መግለጫ በማውጣት ተጠናቅቋል።

ዘጋቢ፦ ተመስገን አሰፋ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“በምድር ንጉሥ፣ በሰማይ ቅዱስ”
Next article“የገበያ ማዕከላትን በማስፋት በከተማ አሥተዳደሮች በሁለት ወር በከተሞች ደግሞ በሦስት ወር አንድ ጊዜ ኢግዚቢሽን እና ባዛር ይዘጋጃል” ኢብራሂም መሐመድ (ዶ.ር)