“ሀገርን መውደዳችን በምንሰጠው የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ልክ ይገለጻል” ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

30

ባሕር ዳር: ሰኔ 12/2016 ዓ.ም (አሚኮ)ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በማኀበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልእክት ሰው ሀገሩን ምን ያህል ይወዳል? ሲባል መልሱ “በበጎ ፈቃድ የሚያገለግላትን ያክል” ነው ብለዋል። “በጎነትና አብሮነት ለኢትዮጵያ ከፍታ” በሚል መሪ ቃል የሚካሄደውን የ2016 ዓ.ም ሀገር አቀፍ የክረምት ወራት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ንቅናቄን ዛሬ መጀመሩን ገልጸዋል፡፡

የበጎ ፈቃድ አገልግሎት መርሐ ግብር ብቻ ሳይኾን እንደ ኢትዮጵያ ባለ በብዝሃነት የደመቀ ሀገር ውስጥ ለጋራ ዕድገት እና የብልጽግና ግባችን መሳካት ወሳኝ መሳሪያ ነው ብለዋል። ይህ አገልግሎት ዜጎች ጊዜያቸውን፣ ጉልበታቸውን፣ ዕውቀታቸውን እና ክህሎታቸውን ለሀገራቸው ዕድገት ያላቸውን ትብብር እና ትጋት የሚያንጸባርቁበት ስለመኾኑም ገልጸዋል።

በመኾኑም በዘንድሮ የክረምት ወራትም አገልግሎቱ ከታጠረበት የክረምት ወቅት በዘለለ በጎ ፈቃድ የሁልጊዜ ተግባር ኾኖ የሚቀጥልበትን ስልት በመንደፍ ታዳጊዎች እና ወጣቶች ወደፊት የሚረከቧትን ብቻ ሳይኾን አሁን የሚኖሩባትንም ሀገር የሚገነቧት ራሳቸው መኾናቸውን በተግባር የሚያሳዩበት እንዲኾን ጥሪያቸውን አቅርበዋል፡፡

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleበመደራጀት እና በኅብረት ለሴቶች ዘርፈ ብዙ ተጠቃሚነት መሥራት እንደሚገባ የአማራ ክልል ሴቶች፣ ህጻናት እና ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ አሳሰበ።
Next articleበሁመራ እና አካባቢው የተቋረጠውን ኃይል መልሶ ለማገናኘት የሚያስችል ሥራ ተጀምሯል።