
አዲስ አበባ: ሰኔ 12/2016 ዓ.ም (አሚኮ)በመርሐ ግብሩ ላይ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህን ጨምሮ ሚኒስትሮች፣ በጎ ፈቃደኞች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶችም ተገኝተዋል። በዘንድሮው የክረምት ወራት በ14 ዘርፎች ከ34 ሚሊዮን በላይ በጎ ፈቃደኞች የሚሳተፉ ሲኾን ከ49 ሚሊዮን በላይ የማኅበረሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ ነውም ተብሏል።
በዘንድሮ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት የሥራ ድግግሞሽን እና የሃብት ብክነትን ማስቀረት ትኩረት እንደሚሰጠው የተገለፀ ሲኾን በገንዘብ ሲተመን 26 ቢሊዮን ብር የሚያወጣ አገልግሎት ለመስጠት መታቀዱም ተገልጿል። የንቅናቄ መድረኩን የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ፣ የሰላም ሚኒስቴር እና የትምህርት ሚኒስቴር በጋራ እንዳዘጋጁትም ተገልጿል።
ዘጋቢ፦ ቤተልሄም ሰለሞን
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!