“ሀገራዊ ብልፅግና ሊረጋገጥ የሚችለው የቤተሰብ ብልፅግናን ማጎልበት ስንችል ነው” አቶ ተመሥገን ጥሩነህ

44

ባሕር ዳር፡ ሰኔ 11/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ሀገራዊ ብልፅግና ሊረጋገጥ የሚችለው የቤተሰብ ብልፅግናን ማጎልበት ስንችል ነው ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመሥገን ጥሩነህ ገለጹ። አቶ ተመሥገን በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በሌማት ትሩፋት እየተከናወኑ ያሉ ስራዎችን ጎብኝተዋል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትሰስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት የሀገር ብልጽግና የሚረጋገጠው የቤተሰብን ብልጽግናን ማጎልበት ሲቻል መሆኑን ገልጸዋል። ለዚህ ደግሞ መንግሥት በሌማት ትሩፋት በርካታ ሥራዎችን እየሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል። ሀገራችን ኢትዮጵያ በተፈጥሮ ሀብት የታደለችና እምቅ አቅም ያላት ሀገር ናት ያሉት አቶ ተመሥገን ለዚህ ማሳያ በሆነችው በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ተገኝተን በሌማት ትሩፋት እየተከናወኑ ያሉ ሥራዎችን ተመልክተናል ብለዋል።

ክልሉ በዚህ መርሀ-ግብር እየሠራቸው ያሉ ተግባራት የሚደነቁ መሆናቸውን ገልጸው በተለይ ደግሞ በአንድ በኩል ሰላምን እያረጋገጡ በሌላ በኩል የልማት ሥራዎችንም ማከናወን እንደሚቻል የታየበት ነው ሲሉ አስረድተዋል። የሌማት ትሩፋት በምግብ ራሳችንን ከመቻል ባሻገር ለበርካታ ዜጎቻን የስራ ዕድልን እየፈጠረ ያለ ተግባር በመሆኑ ተጠናክሮ መቀጠል አለበትም ብለዋል፡፡

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“በከተሞች የተጀመረው የምግብ ዋስትና ፕሮግራም ኑሮ በማሻሻል እና የከተማን ገጽታ በመገንባት ረገድ ፋይዳው የጎላ ነው” የአማራ ክልል ከተማ እና መሠረተ ልማት ቢሮ
Next article“ሩዝን በ5 ዞኖች ለማልማት እየሠራን ነው” ግብርና ቢሮ