
ባሕር ዳር፡ ሰኔ 10/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የማዕከላዊ ጎንደር ዞን በ2016/17 ዓ.ም የምርት ዘመን 17 ነጥብ 5 ሚሊዮን ኩንታል ለማግኘት ታቅዷል። ለእቅዱ መሳካት 580 ሺህ 356 ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ ለማቅረብ እየተሠራ ነው። በዘንድሮው የመኸር ምርት ዘመን ምርት እና ምርታማነትን ለማሳደግ በዋና ዋና ሰብሎች ላይ ትኩረት ተደርጎ እየተሠራ እንደሚገኝ ከዞኑ ግብርና መምሪያ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
ምስል ፦ ከአርካይቭ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!