
ደብረ ብርሃን: ሰኔ 09/2016 ዓ.ም (አሚኮ) 1 ሺህ 445ኛው የዒድ አል አድሃ ዓረፋ በዓል በደብረ ብርሃን ከተማ ሃይማኖታዊ ሥርዓቱ በሚፈቅደው መልኩ ተከብሯል።
በበዓሉ ላይ አሚኮ ያነጋገራቸው የሃይማኖቱ ተከታዮች በዓሉን በአብሮነት እና በመተሳሰብ እንደሚያከብሩት ገልጸዋል።
የደብረ ብርሃን ከተማ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ዋና ጸሐፊ ሀጂ አሊ ሀሰን ከተማ አሥተዳደሩ ለሙስሊሙ ማኅበረሰብ እያደረገ ባለው ቀና ትብብር ምሥጋና አቅርበዋል፡፡
“በዓሉን ስናከብር ያለንን ለሌሎች በማካፈል መኾን አለበት” ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
በበዓሉ አከባበር ላይ የተገኙት የደብረ ብርሃን ከተማ አሥተዳደር ምክትል ከንቲባ ወርቃለማሁ ኮስትሬ ከዚህ በፊት የመስገጃ ቦታ ጥያቄ ሲቀርብ እንደነበር ገልጸው ለመስሊሙ የመስገጃ ቦታ 20 ሺህ ካሬ መሬት መሰጠቱን ተናግረዋል።
የሃይማኖቱ ተከታዮችም ሰላም እንዲጸና የበኩላቸውን ድርሻ እንዲወጡ መልዕክት አስተላልፈዋል።
ዘጋቢ፡- በላይ ተስፋዬ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
