
ባሕር ዳር: ሰኔ 09/2016 ዓ.ም (አሚኮ)1 ሺህ 445ኛው የዒድ አል አድሃ ዓረፋ በዓል የዒድ ሰላት ሃይማኖታዊ ሥርዓቱን በጠበቀ መልኩ መጠናቀቁን የጸጥታ እና ደኅንነት የጋራ ግብረ ኀይል አስታውቋል፡፡
በዓሉ ሃይማኖታዊ ሥርዓቱን ጠብቆ እንዲጠናቀቅ የድርሻቸውን ለተወጡ ሁሉ ግብረ ኃይሉ ምሥጋና አቅርቧል ሰኔ 9 ቀን 2016 ዓ.ም የ1 ሺህ 445ኛው የዒድ አል አደሃ ዓረፋ በዓል የዒድ ሰላት በርካታ የሃይማኖቱ ተከታዮች በታደሙበት በዓሉን በሚመጥን ሃይማኖታዊ ሥርዓት መጠናቀቁን የጸጥታ እና ደኅንነት የጋራ ግብረ ኃይሉ አስታውቋል።
በዓሉ በሰላም እንዲጠናቀቅ አስቀድሞ የተደረገውን ዝግጅት የሚመጥን የተግባር አፈፃፀም ላሳዩ ለመላው የጸጥታ አካላት እንዲሁም ለጸጥታ ኃይሉ ሥራ ተባባሪ በመኾን የድርሻቸውን ለተወጡ የሃይማኖቱ ተከታዬች እና ለሰላም ወዳዱ የከተማው ነዋሪ የጸጥታ እና ደኅንነት የጋራ ግብረ ኃይል ምሥጋና አቅርቧል፡፡
የአዲስ አበባ ፖሊስ በማኅበራዊ ትስስር ገጹ እንዳለው ለመላው የሃይማኖቱቱ ተከታዮች በዓሉ የፍቅር፣ የሰላም እና የጤና እንዲኾን ግብረ ኃይሉ መልካም ምኞቱን ገልጿል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
