
ባሕር ዳር: ሰኔ 09/2016 ዓ.ም (አሚኮ)1ሺህ 445ኛው የዒድ አል አድሃ ዓረፋ በዓል በኮምቦልቻ ከተማ በተለያዩ ሃይማኖታዊ ሥነ-ሥርዓቶች ተከብሯል።
በበዓሉ ላይ የኮምቦልቻ ከተማ እስልምና ጉዳይ ምክር ቤት ሰብሳቢ ሼህ አሕመድ አወል፣ የኮምቦልቻ ከተማ አሥተዳደር ከንቲባ መሐመድአሚን የሱፍን ጨምሮ የመንግሥት የሥራ ኀላፊዎች እና የሃይማኖቱ ተከታዮች በተገኙበት በድምቀት ተከብሯል።
የኮምቦልቻ ከተማ እስልምና ጉዳይ ምክር ቤት ሰብሳቢ ሼህ አሕመድ አወል የዓረፋ በዓልን ስናከብር የተቸገሩትን በመርዳት እና ሃይማኖቱ በሚያዘው መሠረት ሊኾን እንደሚገባ አሳስበዋል።
የኮምቦልቻ ከተማ አሥተዳደር ከንቲባ መሐመድአሚን የሱፍ በበኩላቸው የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል። ከኮምቦልቻ ከተማ አሥተዳደር የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ማኅበራዊ ትስስር ገጽ እንዳገኘነው መረጃ ከንቲባው የዓረፋ በዓልን ስናከብር ሰላም እንዲሰፍን ዱዓ በማድረግ እንዲሁም በዓሉን ስናከብር የተቸገሩ ወገኖችን በመደገፍ ሊኾን ይገባል ብለዋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
