
ባሕር ዳር፡ ሰኔ 09/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አደም ፋራህ የተመራ ከፍተኛ የልዑክ ቡድን ሩሲያ ቭላዲቮስቶክ ከተማ ገብቷል። የልዑክ ቡድኑ ሩሲያ ቭላዲቮስቶክ ከተማ የገባው በብሪክስ ሀገራት የፖለቲካ ፓርቲዎች ዓለም አቀፍ ፎረም ላይ ለመሳተፍ ነው።
ከሰኔ 9/2016 ዓ.ም እስከ ሰኔ 12/2016 ዓ.ም በሚካሔደው እና “ዎርልድ ማጆሪቲ ፎር መልቲፖላር ኦርደር በሚል” መሪ መልዕክት በተዘጋጀው ፎረም ላይ አቶ አደም ፋራህን ጨምሮ በብልጽግና ፓርቲ ጽሕፈት ቤት የፖለቲካ እና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኀላፊ ሰማ ጥሩነህ (ዶ.ር) እና በብልጽግና ፓርቲ የሕዝብ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ኀላፊ አዲሱ አረጋ ይሳተፋሉ።
ኢዜአ እንደዘገበው የልዑክ ቡድኑ ከፎረሙ ጎን ለጎን የብሪክስ አባል ሀገራት ከኾኑ አቻ የፓርቲ አመራሮች ጋር የሁለትዮሽ ውይይት እንደሚያካሂዱም ተገልጿል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
