
ጎንደር: ሰኔ 09/2016 ዓ.ም (አሚኮ)በእስልምና ሃይማኖት ተከታዮች ዘንድ በድምቀት ከሚከበሩ የዒድ በዓላት መካከል የዒድ አል አድሃ ዓረፋ በዓል አንዱ ነው። 1 ሺህ 445ኛው ዓመተ ሂጅራ የዒድ አል አድሃ ዓረፋ በዓል በታሪካዊቷ ጎንደር ከተማ በድምቀት እየተከበረ ነው።
የሃይማኖት አባቶች፣ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኀላፊዎች እና የሃይማኖቱ ተከታዮች በተገኙበት ፋሲለደስ ስታዲየም 1 ሺህ 445ኛው የዒድ አል አድሃ ዓረፋ በዓል በድምቀት እየተከበረ ነው።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
            
		