1 ሺህ 445ኛው የዒድ አል አድሃ ዓረፋ በዓል በደሴ ከተማ እየተከበረ ነው።

11

ደሴ: ሰኔ 09/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የዒድ አል አድሃ ዓረፋ በዓል የአንድነት፣ የመተሳሰብ እና ተለያይቶ የመገናኘት ተምሳሌት መኾኑን የደሴ ከተማ እስልምና ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ሼህ እንድሪስ በሽር ተናግረዋል። በዓሉ ሲከበር የተቸገሩትን በመርዳት ሊኾን ይገባልም ብለዋል ሼህ እንድሪስ በሽር።

የደሴ ከተማ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ሳሙኤል ሞላልኝ ሕዝበ ሙስሊሙ ለክልሉ ሰላም መረጋገጥ የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣም ጠይቀዋል። ሰላም ከሌለ በዓልን በደመቀ መልኩ ማክበር እንደማይቻልም አውስተዋል። ሙስሊሙ ማኅበረሰብ የከተማውን ሰላም የመጠበቅ ተግባሩን አጠናክሮ እንዲቀጥልም ጠይቀዋል።

ሕዝበ ሙስሊሙ የዓረፋ በዓልን ሲያከብር እርስ በእርስ በመደጋገፍ እና አንድነቱን በማጠናከር ሊኾን እንደሚገባ ነው አቶ ሳሙኤል የተናገሩት።

ዘጋቢ፡- አሊ ይመር

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article1 ሺህ 445ኛው የዒድ አል አድሃ ዓረፋ በዓል በአዲስ አበባ በሰላት ሥነ ሥርዓት እየተከበረ ነው።
Next article1 ሺህ 445ኛው የዒድ አል አድሀ ዓረፋ በዓል በጎንደር ከተማ እየተከበረ ነው።