
ባሕር ዳር፡ ሰኔ 08/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ ለመላው የእስልምና ሃይማኖት ተከታዮች በሙሉ “የአንድነት፣ የአብሮነት እና የመረዳዳት እሴት ማሳያ ለኾነው 1ሺህ 445ኛው የዒድ አል አድሃ (ዓረፋ) በዓል እንኳን አደረሳችሁ” ብለዋል።
የዒድ አል አድሃ (ዓረፋ) በዓል ሕዝበ ሙስሊሙ በድምቀት ከሚያከብራቸው በዓላት መካከል አንዱ ነው። በዓሉ በእስልምና ሃይማኖት ተከታዮች ዘንድ ትልቅ ትርጉም ያለው፤ የአንድነትና የአብሮነት እሴቶቻችን በጉልህ የሚንጸባረቁበት በዓል ነው ሲሉም ገልጸዋል።
የተራበን ማብላት፣ የተቸገረን መርዳት እንዲሁም የታረዘን ማልበስ ደግሞ የዓረፋ በዓል ልዩ መገለጫና ቱሩፋት መሆኑን አስገንዝበዋል።
በዓሉን ስናከብር የሀገራችንን ክብር እና የሕዝባችንን አንድነት የሚያጠናክር፤ መተሳሰባችንን እና አብሮነታችንን የበለጠ ከፍ የሚያደርግ እንዲሆንልን ከልብ እመኛለሁ ብለዋል።
መልካም በዓል!
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
