የመንግሥትን የሰላም ጥሪ ተቀብለው ወደ ማኅበረሰቡ የተቀላቀሉ ታጣቂዎች ሌሎችም የእነሱን ፈለግ እንዲከተሉ ጥሪ አቀረቡ።

192

ባሕር ዳር: ሰኔ 08/2016 ዓ.ም (አሚኮ)በማዕከላዊ ጎንደር ዞን በታች አርማጭሆ ወረዳ መንግሥት ያቀረበውን የሰላም ጥሪ የተቀበሉ 16 ታጣቂ ኃይሎች በየቀበሌው በተደረጉ የሕዝብ ለሕዝብ ውይይት እንዲሁም በሀገር በመከላከያ ሰራዊት ያልተቋረጠ ድጋፍ በሰላም ወደ ሕዝቡ ተቀላቅለዋል።

ለተደረገላቸው የሰላም ጥሪ መንግሥትን አመስግነው በቀጣይ ከመንግሥት ጎን ተሰልፈው መደበኛ ሥራቸውን እንደሚጀምሩም ነው የገለጹት። በጫካ ያሉ ሌሎች አካላትም መንግሥት ያመቻቸውን የሰላም ጥሪ ተቀብለው እንዲገቡ ጥሪ
የታች አርማጭሆ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አስማረ የኋላሸት እንደገለጹት በወረዳው ዘላቂ ሰላምን ለማምጣት ከሀገር መከላከያ ሠራዊት፣ ከሃይማኖት አባቶች፣ ከሀገር ሽማግሌዎች እና ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በጋራ እየተሠራ ይገኛል።

የታጠቁ ኃይሎች የመንግሥትን የሰላም ጥሪ ተቀብለው እንደገቡ ገልጸው የሚፈጠሩ ችግሮችን በሰለጠነ እና በሰላማዊ መንገድ በውይይት መፍታት ተገቢ መኾኑንም ጠቁመዋል።
በሌላ በኩል የሀገር ሽማግሌዎች እና የሃይማኖት አባቶች ለዘላቂ ሰላም እየሠሩት ያለው ሥራ አበረታች መኾኑ ተገልጿል::

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“የሀገር ችግር የሚፈታው በትምህርት በመኾኑ በሕጻናት ደረጃ ፆታን መሰረት አድርጎ የሚመጣ ማኅበራዊ ቀውስን መፍታት ያስፈልጋል” አብዱ ሁሴን (ዶ.ር)
Next article“ሕዝበ ሙስሊሙ የዒድ አል አድሃ (ዓረፋ) በዓልን ሲያከብር በአብሮነት እና በመረዳዳት መንፈስ ሊኾን ይገባል” አፈ ጉባኤ ፋንቱ ተስፋዬ