
ባሕር ዳር: ሰኔ 08/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ብሔራዊ ክልል ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ፋንቱ ተስፋዬ የዒድ አል አድሃ (ዓረፋ) በዓልን አስመልክተው የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።
አፈ-ጉባኤዋ ለመላው የእስልምና ሃይማኖት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለ1 ሺህ 445ኛ ዓመተ ሂጅራ የዒድ አል አድሃ (ዓረፋ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ ብለዋል። ሕዝበ ሙስሊሙ የዓረፋ በዓልን ሲያከብር በመተሳሰብ፣ በመረዳዳት እና በመደጋገፍ ሊሆን ይገባል ብለዋል፡፡
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!