አፍሪ ረን ጉባኤ የናይል ተፋሰስ የትብብር ማዕቀፍን ለማጠናከር ጠቃሚ ነው ሲሉ የውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ጃፋር በድሩ ገለጹ።

16

አዲስ አበባ: ሰኔ 08/2016 ዓ.ም (አሚኮ)ሦስተኛው ምክንያታዊ የዓባይ ውኃ አጠቃቀም እና ቀጣናዊ ትብብር (አፍሪ ረን) ጉባኤ በአዲስ አበባ መካሔድ ጀምሯል። ጉባኤው የሚካሔደው “የጋራ ሃብትን በአግባቡ በመጠቀም የጋራ ብልጽግና ለተሻለ ነጋችን እንዲኾን ቀጣናዊ ትብብር እና ትስስር ለምክንያታዊ እና ፍትሐዊ የዓባይ (ናይል) ውኃ አጠቃቀም” በሚል መሪ ሃሳብ ነው እየተካሄደ ያለው። የውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እንዲሁም የውኃ እና ኢነርጂ ሚኒስቴር በጋራ ያዘጋጁት ጉባኤ ነው፡፡

የውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ጃፋር በድሩ ናይል የተፋሰሱን ሀገራት ሕዝቦችን ጥብቅ አንድነት የሚያመጣ ነው ብለዋል። ይህም የነገ እድገት እና ልማታቸውን በአግባቡ የወሰነ ጉዳይ መኾኑን ነው ያነሱት። ይህ ኮንፈረንስ የናይል ተፋሰስ የትብብር ማዕቀፍ አቅምን የሚያሳድግ እንደኾነም አስገንዝበዋል፡፡ ለፖሊሲ አውጭዎችም በተፋሰሱ ሀገራት ላይ የሚያጋጥሙ ችግሮችን እንዲፈቱ የመፍትሄ ሃሳብ የሚሰጥ ነው ብለዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ምሥጋኑ አርጋ የናይል ተፋሰስ ሀገራት የደን ጭፍጨፋን በመከላከል እና የውኃ ምንጭ አቅምን በማጎልበት መሥራት ይገባቸዋል ነው ያሉት። ኢትዮጵያ ታላቁን የሕዳሴ ግድብ በመገንባት ምክንያታዊ እና ፍትሐዊ የውኃ አጠቃቀምን እንዳሳየች አስረድተዋል፡፡

ብሩንዲ የናይል ተፋሰስ ማዕቀፍን ያፀደቀች 5ኛዋ ሀገር በመኾኗ ያላቸውን አድናቆት ገልጸዋል፡፡
በጉባኤው ሁሉም የተፋሰሱ ሀገራት ተወካዮች እየተሳተፉ ነው። ሦስቱም ጉባኤ የተካሄደው በአዲስ አበባ ነው።

ዘጋቢ፡- አንዱዓለም መናን

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“የአየር ትራንስፖርትንና ቱሪዝምን ይበልጥ ለማስተሳሰር እየሠራን ነው”አቶ መስፍን ጣሰው
Next articleየአማራ ክልል ግብርና ቢሮ የክረምት የግብርና ሥራዎች ያሉበትን ደረጃ ገመገመ፡፡