
ባሕር ዳር፡ ሰኔ 08/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በሀጅ ሥነ ሥርዓት በይፋ በተጀመረው የሀጅ ሥነ ሥርአት “የዓረፋ ኹጥባ” ይከናወናል።
“የዓረፋ ኹጥባ” አማርኛን ጨምሮ በ20 ቋንቋዎች እንደሚተረጎም ተገልጿል።
የዓረፋ ኹጥባ ብዙ ተናጋሪ ባላቸው 20 ቋንቋዎች ተተርጉሞ ለ1 ቢሊየን ሰዎች እንዲደርስ ይደረጋል ተብሏል።
በዙል ሂጃ ወር ከሚከናወነው የሃጅ ሥነ ሥርዓት ውስጥ በ9ኛው ቀን የሚፈጸመው “የዓረፋ” ሥነ ሥርዓት እንዱ ነው። ታዲያ ይህ “የዓረፋ ኹጥባ” ሥነ ሥርዓት ዘንድሮ በመላው ዓለም ብዙ ተናጋሪ ባላቸው 20 ቋንቋዎች እንደሚተረጎም የሁለቱ ቅዱሳን መስጂዶች አሥተዳደር ሃራማይን ሸሪፈይን አስታውቋል።
በአረብኛ ቋንቋ የሚከናወነው የዓረፋ ኹጥባ በመላው ዓለም ብዙ ተናጋሪ ባላቸው 20 ቋንቋዎች በመተርጎምም በዓለም ዙሪያ ለ1 ቢሊየን ሰዎች እንዲደርስ እንደሚደረግም ተገልጿል።
የዓረፋ ኹጥባ ተተርጎሙ ከሚተላለፍባቸው ቋንቋዎች መካከል አማርኛ ቋንቋ እንዱ እንደሆነም ተነግሯል።
በተጨማሪም የአረፋ ኹጥባ በእንግሊዘኛ፣ ፈረንሳይኛ፣ ማላይ፣ ኡርዱ፣ ፋርሲ፣ ቻይኒዝ (ማናዳሪን)፣ ተርኪሽ፣ እና የሩሲያኛ ቋንቋዎች እንደሚተረጎም ታውቋል። እንዲሁም፣ ሃውሳ፣ ቤንጋሊ፣ ስዊድሽ፣ ስፓኒሽ፣ ሰዋሂሊ፣ ጣሊያንኛ፣ ፖርቱጋልኛ፣ ቦስኒያን፣ ማላያላም፣ ፍሊፒኖ እና ጀርመንኛ ቋንቋዎችን ይተረጎማል ነው የተባለው።
ከ7 ዓመት በፊት የተጀመረውና በአረብኛ ቋንቋ የሚከናወነው የዓረፋ ኹጥባ በመላው ዓለም ብዙ ተናጋሪ ባላቸው ቋንቋዎች ተተርጉሞ እንዲተላለፍ ሲደረግ ይሄ ለሰባተኛ ጊዜ እንደሆነም ነው የተገለጸው። የ1445ኛው የሀጅ ሥነ ሥርዓት በሳዑዲ አረቢያ መካ በይፋ ተጀምሯል። ዛሬ ሀጃጆች ወደ ሚና ጉዞ ይጀምራሉ ተብሏል። ዓመታዊውን የሀጅ የጸሎት ሥነ ሥርዓት ለመታደም ከ1 ነጥብ 8 ሚሊዮን በላይ ሀጃጆች መካ ከትመዋል።
በተለያዩ የዓለም ሀገራት የሚገኙ ሙስሊሞች የሚታደሙት ዓመታዊ ሥነ ሥርዓት በሃይማኖቱ ዘንድ ትልቅ ስፍራ የሚሰጠው ነው።
አል ዐይን እንደዘገበው ሀጅ ማድረግ እስልምና ከሚያዛቸው 5ቱ መሰረታዊ ሃይማኖታዊ ግዴታዎች መካከል አንዱ ነው።
የዒድ አል አድሃ በዓል ነገ በመላው ዓለም በድምቀት ይከበራል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!