
ባሕር ዳር: ሰኔ 07/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በማዕከላዊ ሸዋ ኮማንድፓስት በሸዋሮቢት ለአምስተኛ ዙር 287 የተሃድሶ ሰልጣኞች ለተከታታይ ስምንት ቀናት የተሃድሶ ስልጠና ወስደው ተመርቀዋል።
የተሃድሶ ሰልጣኞቹ በሰላም ምንነት፣ በሰላም አስፈላጊነት፣ ከግጭት እና ከጦርነት አዙሪት መውጫ መንገዶች፣ የጦርነት እና የግጭት ፈተናዎችን መሻገርያ መንገዶች እና ከሰልጣኞች የሚጠበቁ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ በቂ ስልጠና ተሰጥቷቸዋል።
ከማዕከላዊ ሸዋ ኮማንድፓስት የተሃድሶ ስልጠና ማስተባበሪያ እንደ ተገኘው መረጃ በቀጣይም ወደ ማኅበረሰቡ ሲቀላቀሉ ከዚህ በፊት የነበረውን ጥፋታቸውን በማረም፣ ከአካባቢው ሕዝብ እና መንግሥት ጋር የሠላም አምባሳደር ኾነው እንደሚሠሩም በስልጠናው ማጠቃለያ ላይ መግባባት ተፈጥሯል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!