
ባሕር ዳር: ሰኔ 07/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ ከምዕራብ አማራ የዞን ግብርና መምሪያዎች ጋር የ2016/17 የክልሉ ወቅታዊ የግብርና ልማት ሥራዎች ያሉበትን ሁኔታ እየገመገመ ነው፡፡ በግምገማ መድረኩ ላይ የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ ምክትል ኀላፊ አጀበ ሰንሻው የግብርና ሥራው አሁናዊ ሁኔታውን በትኩረት መገምገም እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡
በግምገማ መድረኩ የሁሉም የምዕራብ አማራ ቀጣና ዞን የግብርና መምሪያ የማኔጅመንት አባላት፣ የቢሮው ማኔጅመንት፣ በመስክ ሥራ ስምሪት ወስደው የነበሩ አባላት እና ሌሎች ባለሙያዎች ተገኝተዋል፡፡ የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ በማኅበራዊ ትስስር ገጹ እንዳለው በመድረኩ የምዕራብ ጎጃም ዞን ግብርና መምሪያ፣ የባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር ግብርና መምሪያ እና የኤስኤምኤስ ቡድን አባላት መልካም የግብርና ልማት ተሞክሮዎች፣ ስኬቶችን እና ያጋጠሙ ችግሮችን አቅርበዋል፡፡
በመድረኩ ትኩረት ከተደረገባቸው ሥራዎች መካከልም፡-
✍️የግብዓት አቅርቦት እና ስርጭት
✍️የምርጥ ዘር አቅርቦት እና ስርጭት
✍️ የ2016/17 የመኽር ምርት ዘመን ሰብል ልማት ሥራዎች
✍️የተፈጥሮ ሃብት ልማት ጥበቃ እና አጠቃቀም
✍️የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ እና ደን ልማት ሥራዎች
✍️ለማዘጋጀት የታቀደ ችግኝ ቦታ ልየታ እና ሌሎች ቅድመ ዝግጅቶች
✍️ የመደበኛ ኮምፖስት ዝግጅት
✍️ ቨርሚል ኮፖስት ዝግጅት
✍️ባዮ ሳላሪ ዝግጅት እና በሌሎች ጉዳዮችም ላይ ወይይት እየተደረገ ነው።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!