ዛሬ ደም በመለገስ የሰዎችን ሕይወት የሚታደጉ በጎ ፈቃደኞች የሚመሠገኑበት የዓለም የደም ልገሳ ቀን ነው።

44

ባሕር ዳር፡ ሰኔ 07/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የዓለም የጤና ድርጅት፣ አጋሮቹ እና ሌሎች የማኅበረሰብ አባላት የዓለም የደም ልገሳ ቀንን አስመልክተው “በመስጠት የመደሰት 20 ዓመታት: ደም ለጋሾችን እናመሠግናለን” በሚለው መሪ ቃል በጋራ ያከብሩታል።

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት 20ኛውን የደም ልገሳ ቀን በተመለከት በማኅበራዊ ሚዲያ ገጹ ባሰፈረው መልእክት የዛሬው ቀን ደም በመለገስ የሰዎችን ሕይወት ለሚታደጉ ደም ለጋሾች ምሥጋና የምናቀርብበት ትልቅ እድል እና አጋጣሚ ነው ብሏል። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የዛሬው የዓለም የደም ልገሰን ቀን አራት አላማዎች አሉት ይላል ፦

1. በዓለም ላይ የሚሊዮኖችን ሕይወት ለሚታደጉ በሚሊየን የሚቆጠሩ ፍቃደኛ ደም ለጋሾችን ማመሥገን፣ እውቅና መስጠት።
2. የደም ልገሳ መርሐግብሮችን በተመለከተ የሚታዩ ስኬቶችን እና ችግሮችን ማሳየት እንዲኹም ምርጥ ተሞክሮዎችን እና ትምህርቶችን ማጋራት
3. በዓለም ያለውን የደም ፈላጊዎች ፍላጎት ለማሟላት መደበኛ እና የማይከፈልበት የደም ልገሳ አስፈላጊ መኾኑን ማስገንዘብ
4. በወጣቶች እና በመላው ማኅበረሰቡ በኩል በመደበኛነት ደም የመለገስ ባሕል እንዲስፋፋ እንዲኹም የደም ለጋሾች ስብጥር እና ቀጣይነት እንዲረጋገጥ መሥራት።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleበሰሜን ወሎ ዞን ራያ አላማጣ ወረዳ የዋጃ እና ጥሙጋ ነዋሪዎች የሕወሀትን ወረራ የሚቃወም ሰላማዊ ሰልፍ አደረጉ።
Next articleየሌማት ትሩፋት ላይ የተሻለ ውጤት እየታየ መኾኑን የዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር አስታወቀ።