የሰላሙ ባለቤት ማኀበረሰቡ እንዲኾን የተሠሩት ሥራዎች ውጤታማ መኾናቸው ተጠቆመ።

18

ባሕር ዳር: ሰኔ 06/2016 ዓ.ም (አሚኮ)በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የከተማ ዘርፍ አስተባባሪ እና የከተማ እና መሠረተ ልማት ቢሮ ኀላፊ አሕመዲን ሙሐመድ (ዶ.ር.)፣ የኮማንዶ እና የአየር ወለድ ጠቅላይ መምሪያ ምክትል አዛዥ ብርጋዴር ጄነራል አበባው ሰይድ እንዲኹም ሌሎች የጸጥታ አባላት እና አመራሮች በመድረኩ ላይ ተገኝተዋል።

የአማራ ክልል ሰላም እና ደኅንነት ቢሮ ምክትል ኀላፊ በሪሁን መንግስቱ እንዳነሱት ሰላምን ለማጽናት እና ውጤታማ የማኀበረሰብ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ በትኩረት ይሠራል ብለዋል። የሰላሙ ባለቤት ማኀበረሰቡ እንዲኾን የተሠሩት ሥራዎች ውጤታማ መኾናቸውን ጠቁመዋል። የኮማንዶ እና የአየር ወለድ ጠቅላይ መምሪያ ምክትል አዛዥ ብርጋዴር ጄነራል አበባው ሰይድ እንዳሉትም በቀጣናው የነበረውን የሰላም ችግር በተቀናጀ መዋቅር መምራት መቻሉን ጠቅሰው አሁንም የሕግ ማስከበር ሥራውን አጠናክሮ መፈጸም ያስፈልጋል ብለዋል።

የአካባቢውን የጸጥታ ችግር በማስተካከል ማኀበረሰቡ ወደ ተሟላ ሰላም እንዲሸጋገር ይሠራልም ብለዋል። በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የከተማ ዘርፍ አስተባባሪ እና የከተማ እና መሠረተ ልማት ቢሮ ኀላፊ አሕመዲን ሙሐመድ (ዶ.ር.) እንዳነሡትም የሕግ ማስከበር ሥራውን በየደረጃው በተገቢው እየገመገሙ መምራት እንደሚጠይቅ ገልጸዋል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየክረምቱን መግባት ተከትሎ ሊከሰት የሚችለውን የጎርፍ እና የመሬት መንሸራተት ለመከላከል ቅድመ ዝግጅት ማድረግ እንደሚገባ ተጠየቀ።
Next article“የጎርፍ አደጋ እንዳይደርስ ከወዲሁ ጥንቃቄ ማድረግ ተገቢ ነው” የምሥራቅ አማራ ሚቲዎሮሎጂ አገልግሎት ማዕከል