አቢሲኒያ ባንክ ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎት ለሁለተኛ ጊዜ ያዘጋጀውን አሚን አዋርድ የሥራ ፈጠራ ውድድር ይፋ አደረገ፡፡

24

አዲስ አበባ: ሰኔ 06/2016 ዓ.ም (አሚኮ) አቢሲኒያ ባንክ ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎት በኩል ለሁለተኛ ጊዜ ያዘጋጀውን አሚን አዋርድ የሥራ ፈጠራ ውድድር አስመልክቶ መግለጫ ሰጥቷል። በመግለጫውም የመጀመሪያው አሚን አዋርድ የሥራ ፈጠራ ውድድር ችግር ፈች የኾኑ ሃሳቦች የተካተቱበት መኾኑ ተገልጿል፡፡

በውድድሩም የተቀመጡትን የመለያ መስፈርት ያሟሉ 180 ተወዳዳሪዎች ሀሳቦቻቸው በውድድሩ ተሳታፊ ለመኾን መመረጣቸው ነው የተብራራው፡፡ ከተመረጡት ውስጥ 126 ተወዳዳሪዎች በቴክኖሎጂ ግብዓት፣ በግብርና ምርቶች ማሳደጊያ፣ በግንባታ ቴክኖሎጅ፣ በትምህርት እና ጤና ሃሳባቸውን ማቅረብ እንደቻሉ ተጠቅሷል።

አቢሲኒያ ባንክ ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎት በኩል ለሁለተኛ ጊዜ ያዘጋጀውን አሚን አዋርድ የሥራ ፈጠራ ውድድርንም አስመልክቶ ማብራሪያ ሰጥቷል። ውድድሩ ችግር ፈች የኾኑ ሃሳቦች የተካተቱበት መኾኑ ተገልጿል። በውድድሩም የተቀመጡትን የመለያ መስፈርት ያሟሉ 180 ተወዳዳሪዎች ሃሳቦቻቸውን አቅርበው በውድድሩ ተሳታፊ እንዲኾኑ ተመርጠዋል፡፡

ከተመረጡት ውስጥ 126 ተወዳዳሪዎች በቴክኖሎጂ ግብዓት፣ በግብርና ምርቶች ማሳደጊያ፣ በግንባታ ቴክኖሎጅ፣ በትምህርት እና ጤና ሃሳባቸውን ማቅረብ እንደቻሉ ተጠቅሷል። በውድድሩም ከ126 ተወዳደሪዎች መካከል ከ1ኛ እስከ 5ኛ ደረጃን በማግኘት አሸናፊ ለኾኑ ከ200 ሺህ እስከ 1ሚሊዮን ብር የሥራ ማስኬጃ ሽልማት እንደሚያበረክት ነው የተገለጸው።

የሽልማቱ ሥነ ሥርዓቱም ሰኔ 9/2016 ዓ.ም በስካይላይት ሆቴል ይከናወናል ተብሏል።

ዘጋቢ፡- ራሔል ደምሰው

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleኢንደስትሪ ሚኒስቴር በሀገር ውስጥ ለሳፋሪ አገልግሎት የሚውሉ መኪናዎችን በናሙናነት ለጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት አስረከበ።
Next articleሀገር አቀፍ የኪነ-ጥበብ እና ሥነ-ጥበብ የፈጠራ እና ትዕይንት ውድድር ሊካሄድ ነው፡፡