የጎንደር ከተማ ሕዝብ በወቅታዊ የሰላም እና የጸጥታ፤ የልማት እና የመልካም አሥተዳደር ጉዳዬች ላይ እየመከረ ነው፡፡

27

ጎንደር: ሰኔ 05/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ምክክሩ “ሀገራዊ እሴቶች እና ብሔራዊ መግባባት ለሰላም ግንባታ” እንጠቀም በሚል መሪ መልዕክት ነው እየተካሄደ የሚገኘው። በምክክሩ ከጎንደር ከተማ ከተለያዩ ክፍለ ከተሞች የተውጣጡ የቀበሌ ምክር ቤት አባላት እና የተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች ተሳታፊ ኾነዋል።

ምክክሩ በአራዳ፣ ዞብል፣ ጃንተከል እና ፋሲል ክፍለ ከተሞች ነው እየተካሄደ የሚገኘው፡፡ በወቅታዊ የሰላም እና ጸጥታ፤ የልማት እና የመልካም አሥተዳደር ጉዳዬች ላይ ከሕዝብ እንደራሴዎች ጋር ነው ምክክሩ እየተካሄደ የሚገኘው።
ምክክሩ ለሦስት ቀናት እንደሚቀጥልም ለማወቅ ተችሏል።

ዘጋቢ፡- ዳንኤል ወርቄ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleበአማራ ክልል በተለያዩ አካባቢዎች ሲሰጥ የነበረው የ8ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና በሰላም ተጠናቀቀ፡፡
Next article“ተጋግዞ ችግርን በመፍታት ከግጭት አስተሳሰብ መውጣት ያስፈልጋል” ድረስ ሳህሉ (ዶ.ር )