በአዊ ብሔረሰብ አሥተዳደር ሲሰጥ የቆየው ክልላዊ የ8ኛ ክፍል ፈተና በሰላም ተጠናቅቋል፡፡

11

ባሕር ዳር: ሰኔ 05/2016 ዓ.ም (አሚኮ)

የብሔረሰብ አሥተዳደሩ ትምህርት መምሪያ ኀላፊ ደስታው አለሙ ከሰኔ 4/2016 ዓ.ም ጀምሮ በ1መቶ 19 የፈተና ጣቢያዎች የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ሲሰጥ መቆየቱን ተናግረዋል። ከ8 ሺህ በላይ የሚሆኑ ተማሪዎችም ፈተናቸውን በወቅቱ ተገኝተው መፈተናቸውንም ገልጸዋል።

ለሁለት ተከታታይ ቀናት ሲሰጥ የነበረው ፈተና ያለምንም ችግር በሰላም መጠናቀቁን የገለጹት መምሪያ ኀላፊው በፈተናው ሂደት ተሳትፎ ለነበራቸው አካላት ሁሉ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

ሳሙኤል አማረ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየኮንትራት ቅጥር ማስታወቂያ ! ጊዜያዊ የረዥም ጊዜ/ የኮንትራት ቅጥር ማስታወቂያ፦
Next articleበአማራ ክልል በተለያዩ አካባቢዎች ሲሰጥ የነበረው የ8ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና በሰላም ተጠናቀቀ፡፡