
ባሕር ዳር: ሰኔ 05/2016 ዓ.ም (አሚኮ)
በባሕርዳር ከተማ በ47 ትምህርት ቤቶች ሲሰጥ የቆየው የ8ኛ ክፍል ማጠቃለያ ፈተና ተጠናቅቋል። በባሕርዳር ከተማ በ2016 የትምህርት ዘመን የ8ኛ ክፍል ፈተናን 5ሺ 988 ተማሪዎች መውሰዳቸው ነው የተገለጸው፡፡
የባሕርዳር ከተማ አሥተዳደር ትምህርት መምሪያ ኀላፊ ኃይለማርያም እሸቴ ለመፈተን ከተመዘገቡት ተማሪዎች ውስጥ 96 ነጥብ 89 ተፈታኞች በተረጋጋ ሁኔታ መፈተናቸውን ተናግረዋል።
የባሕርዳር ከተማ የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን መምሪያ በማኅበራዊ ትስስር ገጹ እንዳለው ፈተናው በስኬት እንዲጠናቀቅ የከተማ አሥተዳደሩ መሪዎች፣ የትምህርት አመራሩ እና ሙያተኞች፣ ርዕሳነ መምህራን፣ ሱፐርቫይዘሮች፣ መምህራን እና የጸጥታ ኀይሉ ላደረጉት ርብርብ ምሥጋና አቅርበዋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!