በደሴ ከተማ አስተዳደር የ8ኛ ክፋል መልቀቂያ ማጠቃለያ ፈተና በሰላም ተጠናቅቋል።

12

ባሕር ዳር: ሰኔ 05/2016 ዓ.ም (አሚኮ)የደሴ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ሰይድ የሱፋ የ8ኛ ክፋል መልቀቂያ ማጠቃለያ ፈተና ያለምንም ችግር መጠናቀቁን ተናግረዋል። ምክትል ከንቲባው ፈተናው በስኬት እንዲጠናቀቅ አስተዋጽኦ ላበረከቱ የከተማዋ አመራሮች፣ የጸጥታ መዋቅር፣ የትምህርት ቤት ሱፐርቫይዘሮች፣ ረዳት መምህራን፣ መምህራን፣ የተማሪ ወላጅ መምህር ሕብረት እና ተማሪዎች ምስጋና አቀርባለሁ ብለዋል።

ከደሴ ከተማ አስተዳደር ኮምዩኒኬሽን መምሪያ እንዳገኘነው መረጃ ምክትል ከንቲባ ሰይድ የሱፋ በመጨረሻም በቀጣይ የ6ኛ እና 12ኛ ክፋል ፈተናዎችን በስኬት በማጠናቀቅ ለትምህርት ጥራት የበኩላችንን ልንወጣ ይገባል ብለዋል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“የማይካድራ ከተማ ሰማዕታትን መቼም አንረሳቸውም ጊዜው የሥራና የትግል ነው” አሸተ ደምለው
Next articleበባሕርዳር ከተማ ሲሰጥ የቆየው የ8ኛ ክፍል ፈተና ተጠናቀቀ፡፡