በማዕከላዊ ጎንደር ዞን በታች አርማጭሆ ወረዳ መንግሥት ያቀረበውን የሰላም ጥሪ የተቀበሉ 14 ታጣቂ ኀይሎች ማኅበረሰቡን ተቀላቀሉ።

30

ባሕር ዳር፡ ሰኔ 05/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የመንግሥት የሰላም ጥሪን የተቀበሉት ታጣቂዎቹ ለሰላም ዝግጁ መኾናቸውን ተናግረዋል። ለተደረገላቸው የሰላም ጥሪ መንግሥትን አመሥግነው በቀጣይ ከመንግሥት ጎን ተሰልፈው መደበኛ ሥራቸውን እንደሚጀምሩም ነው የገለጹት።
ሌሎች አካላትም መንግሥት ያመቻቸውን የሰላም ጥሪ ተቀብለው እንዲገቡ ጥሪ አቅርበዋል።

የታች አርማጭሆ ወረዳ ሰላምና ደህንነት ጽ/ቤት ኃላፊ ፍቃዱ ካሳ በወረዳው ዘላቂ ሰላምን ለማምጣት ከሀገር መከላከያ ሠራዊት፣ ከሃይማኖት አባቶች፣ ከሀገር ሽማግሌዎች እና ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በጋራ እየተሠራ እንደሚገኝ አንስተዋል። የታጠቁ ኃይሎች የመንግሥትን የሰላም ጥሪ ተቀብለው እንደገቡ ገልጸው የሚፈጠሩ ችግሮችን በሠለጠነ መንገድ በውይይት መፍታት ተገቢ መኾኑንም ጠቁመዋል።

በሌላ በኩልም የሀገር ሽማግሌዎች እና የሃይማኖት አባቶች ለዘላቂ ሰላም እየሠሩት ያለው ሥራ አበረታች መኾኑ ተገልጿል። የ78ኛ ክፍለ ጦር ዋና አዛዥ ኮሎኔል ግርማ መሀመድ ለሰላም ዘብ መቆም፣ መረዳዳት እና መደጋገፍ እንዲሁም ለሰላም መዘመር ያለበት የሀገር መከላከያ ሠራዊት ብቻ አለመኾኑን በመገንዘብ ሁሉም ሰላም ወዳድ የኅብረተሰብ ክፍል ሰላምን ለማስፈን የበኩሉን ሁሉ እንዲወጣ አሳስበዋል፡፡

የማእከላዊ ጎንደር ዞን መንግሥት ኮሙኒኬሽን መረጃ እንደሚያሳየው፤ ሠራዊቱም የሀገርን ዳር ድንበር ከመጠበቅ በተጨማሪ የሀገሪቱን የውስጥ ችግሮችን ሰላም ለማድረግ በየግዳጅ የማኅበረሰቡን ሰቆቃ በመታደግ አለኝታነቱን ያስመሰከረ የሕዝቡን ሰላም ለማምጣት እና የሕግ የበላይነትን ለማስከበር ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይል በፅናት የሚታገል መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየቻግኒ ከተማ ሕዝብ በዘላቂ ሰላም ዙሪያ እየመከረ ነው፡፡
Next article“የማይካድራ ከተማ ሰማዕታትን መቼም አንረሳቸውም ጊዜው የሥራና የትግል ነው” አሸተ ደምለው