የቻግኒ ከተማ ሕዝብ በዘላቂ ሰላም ዙሪያ እየመከረ ነው፡፡

16

ባሕር ዳር: ሰኔ 05/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በአዊ ብሔረሰብ አሥተዳደር የሕግ ማስከበር ግዳጁን እየተወጣ የሚገኘው ኮር የዞኑን ሰላም በዘላቂነት ለማረጋገጥ ከተለያዩ የማኅበረሰብ ክፍሎች ጋር ምክክር እያካሄደ ነው፡፡ በቻግኒ ከተማ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በጽንፈኞች እና በፀረ ሰላም ኀይሎች የሚስተዋለውን ሕገ-ወጥ ድርጊት ከጸጥታ ኀይሉ ጋር ኾኖ ለመከላከል እና ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታት ከሀገር ሽማግሌዎች፣ ከሃይማኖት አባቶች እና ከወጣቶች ጋር ምክክር ማድረግ አሥፈላጊ መኾኑ ተገልጿል፡፡

የምክክር መድረኩን የመሩት የአዊ ብሔረሰብ አሥተዳደር ዋና አሥተዳዳሪ ቴድሮስ እንዳለው ቻግኒ የብሔር እና የሃይማኖት ማዕከል ናት ብለዋል፡፡ ዋና አሥተዳዳሪው የቻግኒ ሕዝቦች ለዘመናት በጋራ አብረው ኖረውባታል አሁን ላይ ግን የጥፋት ቡድኑ ተላላኪዎች በሕዝቡ ውስጥ የበሬ ወለደ ወሬዎችን እየነዙ ሕዝቡን ለመከፋፈል እና ሕይወቱን እንዳይመራ እያደረጉ በመኾኑ በጋራ ችግሩን ማስወገድ ያስፈልጋል ነው ያሉት።

የውይይቱ ተሳታፊዎች በሰጡት አስተያየት ቻግኒ በርካታ ብሔሮች እና ሃይማኖቶች ተከባብረው የሚኖሩባት ከተማ መኾኗን ገልጸዋል፡፡ የመከላከያ ሠራዊት በማኅበራዊ ትስስር ገጹ እንዳለው ጥቂት ቡድኖች የጥፋት አጀንዳቸውን ለማሳካት ሕዝቡን በሐሰት ወሬ ውዥንብር ውስጥ እንዲገባ እየሠሩ በመኾኑ እነዚህን ቡድኖች ለሕግ አካል አሳልፎ በመስጠት ከጸጥታ አካላት ጋር እየሠሩ እንደኾነም ነው ያስገነዘቡት፡፡

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleበመከላከያ ሠራዊት ስም እና ማዕረግ ለዘረፋ የተሰማሩ የጽንፈኛው አባላት በቁጥጥር ስር ዋሉ።
Next articleበማዕከላዊ ጎንደር ዞን በታች አርማጭሆ ወረዳ መንግሥት ያቀረበውን የሰላም ጥሪ የተቀበሉ 14 ታጣቂ ኀይሎች ማኅበረሰቡን ተቀላቀሉ።