
የክፍለጦሩ አዛዥ ኮሎኔል አለም ታደለ አንድ ሬጅመንት በሰሜን ጎጃም ጎንጂ ቆለላ ወረዳ ብራቃትና ዴንሳ ባታ ቀበሌ ሕዝቡን በዘረፋ ሲያሰቃዩ በነበሩ የፅንፈኛው አባላት ላይ በወሰደው እርምጃ 12 ክላሽ 04 ሽጉጥ 08 የቃታ መሳሪያ 02 ጀኔነተር 03 ሞተር ሳይክልና 10 ጀሪካን ቤንዝን እንዲሁም የተለያዩ የመሳሪያ መጠገኛ ስፔር ፓርቶችን ማርከዋል ብለዋል።
ኮሎኔል አለም እንደተናገሩት የክፍለ ጦሩ ሬጅመንት በሰሜን ጎጃም ዞን ጎንጂ ቆለላ ወረዳ በተለያዩ ቀበሌዎች ግዳጁን በመፈጸም የፅንፈኛውን ቡድን መንጥሮ እርምጃዎችን ወስዷል። በዚህም አንፃራዊ ሰላም ማስፈን መቻሉን ነው የገለጹት።
የአማራ ሕዝብ ሰላምን ሙሉ ለሙሉ ለማረጋገጥ ሰራዊታችን ቀንና ሌሊት ያለ እረፍት በቁርጠኝነት እየሠራ ይገኛል። የሰላሙ ባለቤት ኅብረተሰቡ በመሆኑ ከፌዴራልና ከክልል የፀጥታ ኀይሎች ጎን በመሆን የተለመደ አጋርነቱን አጠናክሮ መቀጠል ይኖርበታል ብለዋል።
መረጃው የጎጃም ኮማንድ ፖስት ነው