
ባሕር ዳር: ሰኔ 04/2016 ዓ.ም (አሚኮ)የጎንደር ዩኒቨረሲቲ በተለያዩ ጊዚያት ዩኒቨርሰቲውን ያገለገሉ እና በጡረታ የተገለሉ ባለውለታዎችን ለማስታወስ እና ለማመስገን በየዓመቱ የጡረተኞች ቀንን ያከብራል። በዚህ ዓመትም 4ኛውን የዩኒቨርሲቲው የጡረተኞች ቀን በተለያዩ ዝግጅቶች አክብሯል፡፡
በመርሐ ግብሩ ላይ የጎንደር ዩኒቨርሰቲ ፕሬዚዳንት አስራት አፀደወይን (ዶ.ር) ጨምሮ የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች፣ በጡረታ በክብር የተሰናበቱ የዩኒቨርሲቲው ጡረተኞች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡ በመርሐ ግብሩ የጎንደር ዩኒቨርስቲ ፕሬዘዳንት አስራት አጸደወይን (ዶ.ር) “በተሰማሩበት የሥራ እና የሙያ ዘርፍ በታማኝነት አገልግሎ ተቋምን ለተተኪ ትውልድ ማስተላለፍ እድለኝነት ነው” ብለዋል።
ዶክተር አስራት የተለያዩ ግልጋሎቶችን በመስጠት ተቋሙን ለዚህ ታላቅ ደረጃ ላበቁት ጀግኖች የተለያዩ ጥቅማ ጥቅሞችን እንዲያገኙ ውሳኔዎችን መተላለፉን ተናግረዋል፡፡ ከጎንደር ዩኒቨርሲቲ ማኅበራዊ የትስስር ገጽ እንዳገኘነው መረጃ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሆሲፒታል ከተመሠረተ 100 ዓመት ኾኖታል። ዩኒቨርሲቲው ከተመሠረተ ደግሞ 70 ዓመት አስቆጥሯል፡፡
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!