
ባሕር ዳር: ሰኔ 04/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ ከሩሲያ አቻቸው ሰርጌይ ላቭሮቭ ጋር ከብሪክስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ስብሰባ ጎን ለጎን ተወያይተዋል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ እንደሚያመላክተው ሁለቱ ሚኒስትሮች የተወያዩት በብሪክስ ማዕቀፍ ስር በመኾን ትብብርን ማጠናከር በሚቻልባቸው መንገዶች ላይ ነው።
በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ታሪካዊ የሁለትዮሽ ግንኙነት የበለጠ ለማስፋት ያላቸውን ቁርጠኝነትም በውይይታቸው አረጋግጠዋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!