
ባሕር ዳር: ሰኔ 04/2016 ዓ.ም (አሚኮ)ምክር ቤቱ በ31ኛ መደበኛ ስብሰባው ሦስት የተለያዩ ረቂቅ አዋጆችን መርምሮ ለሚመለከታቸው ቋሚ ኮሚቴዎች መርቷል። ምክር ቤቱ የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የንብረት ማስመለስ ረቂቅ አዋጅን እና የነዳጅ ውጤቶችን የግብይት ሥርዓት ለመደንገግ የቀረበ ረቂቅ አዋጅን መርምሮ ለዝርዝር እይታ ለሚመለከተው ቋሚ ኮሚቴ መርቷል፡፡
ምክር ቤቱ በወንጀል የተገኘ ንብረት ሕጋዊ ማስመሰል እና ሽብርተኝነትን በገንዘብ የመርዳት ወንጀልን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር የቀረበ ረቂቅ አዋጅንም መርምሮ ለዝርዝር እይታ ወደሚመለከተው ቋሚ ኮሚቴ መርቷል:: በምክር ቤቱ የመንግሥት ረዳት ተጠሪ ሚንስቴር ዴኤታ ወይዘሮ መሠረት ኃይሌ ረቂቅ አዋጆቹን አስመልክቶ አጭር ማብራሪያ አቅርበዋል። የንብረት ማስመለስ ረቂቅ አዋጅ ዓላማ የወንጀል ፍሬ የኾኑ ንብረቶችን እና ገንዘቦችን ውጤታማ በኾነ መልኩ ለመያዝ ወይም ለመውረስ እንዲኹም ለማስተዳደር የሚያስችል መኾኑን ገልጸዋል።
ረቂቁ ማንኛውም ሰው በሕገ ወጥ ድርጊት ጥቅም እንዳያገኝ ለማድረግ የሚያስችል የንብረት ማስመለስ እና ማስተዳደር ሥርዓት ለመዘርጋት እንደሚያስችል ተጠቁሟል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!