
ባሕር ዳር: ሰኔ 04/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አሥተዳደር ጋዝጊብላ ወረዳ የዛሮታ 1ኛና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ክልል አቀፍ የ8ኛ ክፍል ተማሪዎች እየተፈተኑ ነው።
ክልል አቀፍ የ8ኛ ክፍል ፈተናውን የብሔረሰቡ አሥተዳዳሪ ኀይሉ ግርማይን ጨምሮ የትምህርት መምሪያው የሥራ ኀላፊዎች በቦታው ተገኝተው ምልከታ እያደረጉ መኾኑን ከብሔረሰብ አሥተዳደሩ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!