
ባሕር ዳር: ሰኔ 04/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ኢትዮጵያ እና ደቡብ አፍሪካ ከወራት በፊት የተፈረመውን ስትራቴጂያዊ አጋርነት ተግባራዊ ማድረግ በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይ መክረዋል፡፡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ ከደቡብ አፍሪካ የዓለም አቀፍ ግንኙነት እና ትብብር ሚኒስትር ናሌዲ ፓንዶር ጋር በሁለትዮሽ እና በጋራ ጉዳዮች ላይ ውይይት አድርገዋል።
ሁለቱ ሚኒስትሮች በሁለቱ ሀገራት መካከል ከወራት በፊት የተፈረመው ስትራቴጂያዊ አጋርነት ስምምነትን ተግባራዊ ማድረግ በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይም ሃሳብ ተለዋውጠዋል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በማኅበራዊ ትስስር ገጹ እንዳለው ውይይቱ የተደረገው በሩሲያ እየተካሄደ ከሚገኘው የብሪክስ የውጭ ጉዳይ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሚኒስትሮች ሥብሠባ ጎን ለጎን ነው።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!