ምክትል ፕሬዚዳንት እና ሌሎች ዘጠኝ ሰዎች የጫነውን የወታደራዊ አውሮፕላን የማፈላለጉ ሥራ ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡

14

ባሕር ዳር: ሰኔ 04/2016 ዓ.ም (አሚኮ)የማላዊ የፕሬዚዳንት ጽሕፈት ቤት የሀገሪቱን ምክትል ፕሬዚዳንት እና ሌሎች ዘጠኝ ሰዎችን የጫነ የወታደራዊ አውሮፕላን መሰወሩን አስታውቋል።

የ51 ዓመቱን ምክትል ፕሬዚዳንት ሳኡሎስ ቺሊማን እና ሌሎችንም ሰዎች ጭኖ ከዋና ከተማው ሊሎንግዊ የተነሳው አውሮፕላን ጉዞውን ወደ ምዙዙ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ አድርጎ ነበር የተነሳው። ከ45 ደቂቃ በኋላም እንደሚደርስ ነበር የሚጠበቀው።

አውሮፕላኑ ከመዲናዋ ሊሎንግዊ የተነሳው ትላንት ጠዋት 3:00 ሰዓት ላይ ነበር። የፕሬዚዳንት ጽሕፈት ቤት ባወጣው መግለጫ መሠረት አውሮፕላኑ ከራዳር እይታ ከወጣ በኋላ የአቬሽን ግንኙነቱ እንደተቋረጠ ተጠቁሟል።

አልጀዚራ እንደዘገበው ፕሬዚዳንት ቻክሜራ ፍለጋው ተጠናክሮ እንዲቀጥል ስምሪት ቢሰጡም እስከ አሁን ፍንጭ አልተገኘም።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየወጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ ከቻይና አቻቸው ጋር ተወያዩ።
Next articleኢትዮጵያ እና ደቡብ አፍሪካ በስትራቴጂያዊ አጋርነት ዙሪያ መከሩ።