የወጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ ከቻይና አቻቸው ጋር ተወያዩ።

20

ባሕር ዳር: ሰኔ 04/2016 ዓ.ም (አሚኮ)የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ ከቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ይ ጋር ተወያይተዋል።

ሚኒስትሮቹ የሁለቱን ሀገራት “በሁኔታዎች የማይለዋወጥ ስትራቴጂያዊ አጋርነት” በተለያዩ መስኮች የበለጠ ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ተነጋግረዋል።

እንደ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ውይይቱ የተደረገው በሩሲያ እየተካሄደ ከሚገኘው የብሪክስ የውጭ ጉዳይ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሚኒስትሮች ስብሰባ ጎን ለጎን ነው።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየግዥ እና ንብረት አሥተዳደር አዋጅ ጸደቀ፡፡
Next articleምክትል ፕሬዚዳንት እና ሌሎች ዘጠኝ ሰዎች የጫነውን የወታደራዊ አውሮፕላን የማፈላለጉ ሥራ ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡