ከ2010 እስከ 2015 ዓመተ ምህረት የተላለፉ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ውሳኔዎችን የያዘ መጽሐፍ ይፋ ኾነ።

71

ባሕር ዳር: ሰኔ 04/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ሰብሳቢነት የሚኒስትሮች ምክር ቤት የ100 ቀናት ግምገማ ቁልፍ የሆኑ ሴክተሮችን አፈጻጸም በጥልቀት በመመልከት ማካሄድ ጀምሯል።

ከግምገማ መድረኩ በተጓዳኝ ከ2010 እስከ 2015 ዓመተ ምህረት የተላለፉ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ውሳኔዎችን የያዘ መጽሐፍ ይፋ ኾኗል። ይህ መጽሐፍ በተጠቀሰው ዘመን የተላለፉ የፖሊሲ ውሳኔዎችን በዝርዝር ያመለክታል።

የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ፕሬስ ሴክሬታሪያት ክፍል የሚያከናውነው የመሰነድ ተግባር አንዱ የኾነው ይህ መጽሐፍ ለታሪክ ስነዳ እና መረጃውን ለሚሹ ሁሉ ጠቃሚ የኾነ የሰነድ ዝግጅት ሥራ አካል መኾኑ ተገልጿል።

ዛሬ ይፋ የኾነው መጽሐፍ ውስን ቅጂዎች ለፌደራል እና ለክልል ተቋማት እንደሚሠራጩ ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። መረጃውን ለሚፈልጉ ሁሉ ደግሞ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ድረገጽ ላይ የሚጫን እንደሚኾንም ተገልጿል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“ከ4 ሺህ በላይ ተማሪዎች የ8ኛ ክፍል ፈተናን እየወሰዱ ነው” የደሴ ከተማ አሥተዳደር
Next articleየግዥ እና ንብረት አሥተዳደር አዋጅ ጸደቀ፡፡