
ባሕር ዳር: ሰኔ 04/2016 ዓ.ም (አሚኮ)የሚኒስትሮች ምክር ቤት የበጀት ዓመቱ ከመጠናቀቁ በፊት የመጨረሻ የኾነውን የ100 ቀናት ግምገማ ዛሬ ጠዋት ጀምሯል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) በማኅበራዊ የትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልእክት ዛሬ ጠዋት የዘንድሮው የበጀት ዓመት ከመጠናቀቁ በፊት የመጨረሻ የኾነውን የሚኒስትሮች ምክር ቤት የመቶ ቀናት ግምገማ ጀምረናል ብለዋል። እንደሁልጊዜው የየሴክተሮችን አፈፃፀም እንገመግማለን ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ክፍተቶችን እናጤናለን፤ በጥንካሬዎች ላይ ለቀጣይ ሥራዎች እንነሳለን ብለዋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!