
ደብረ ማርቆስ፡ ሰኔ 04/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ዘላቂ ሰላምን በማጽናት በዘላቂነት እግር መትከል በሚል መሪ መልዕክት የምሥራቅ ጎጃም ዞን እና የደብረ ማርቆስ ከተማ አሥተዳደር የሥራ ኀላፊዎች ከክልሉ ከፍተኛ መሪዎች እና ከሕዝብ ተወካዮች ጋር በደብረ ማርቆስ ከተማ እየመከሩ ነው።
በምክክሩ ላይ በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የገጠር ዘርፍ አስተባባሪ እና የአማራ ክልል የግብርና ቢሮ ኀላፊ ድረስ ሳህሉ (ዶ.ር) ባለፉት 10 ወራት በክልሉ የተከሰተውን የግጭት ምእራፍ በመዝጋት የሕዝቡን የሰላም ፍላጎት እና የመልማት ጥያቄዎች ለመፍታት በቁርጠኝነት መንቀሳቀስ ይገባል ብለዋል።
ዶክተር ድረስ በየደረጃው የሚገኙ የመንግሥት የሥራ ኀላፊዎች ሕዝቡን በማስተባበር ሰላምን ማረጋገጥ እና በጸጥታ ችግር ምክንያት የተጓተቱ የልማት እና የመልካም አሥተዳደር ተግባራትን ለማነቃቃት በትጋት ሊሠሩ እንደሚገባ አሳስበዋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!