ከ8 ሺህ በላይ ተማሪዎች የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና እየወሰዱ መኾናቸውን የአዊ ብሔረሰብ አሥተዳደር ትምህርት መምሪያ አስታወቀ።

16

እንጅባራ፡ ሰኔ 04/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በአማራ ክልል ከሰኔ 4/2016 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት ሁለት ተከታታይ ቀናት የ8ኛ ክፍል ተማሪዎች ክልላዊ ፈተና እየተሰጠ ነው። በአዊ ብሔረሰብ አሥተዳደርም ከ8 ሺህ በላይ የሚኾኑ ተማሪዎች ለፈተና መቀመጣቸውን ነው የብሔረሰብ አሥተዳደሩ ትምህርት መምሪያ ያስታወቀው።

የብሔረሰብ አሥተዳደሩ ትምህርት መምሪያ ኀላፊ ደስታው ዓለሙ የመማር ማስተማር ሥራ በሚካሄድባቸው በሁሉም ትምህርት ቤቶች ተማሪዎች የተሻለ ውጤት እንዲያስመዘግቡ የሚያስችሉ ሥራዎች በስፋት ሢሠሩ መቆየታቸውን ተናግረዋል። ከሰኔ 4/2016 ዓ.ም ጀምሮ በሚሰጠው ክልላዊ ፈተና 119 የሚኾኑ ትምህርት ቤቶች ፈተናውን እየሰጡ እንደሚገኙ መምሪያ ኀላፊው ገልጸዋል።

የፈተና አሰጣጡን ጤናማ ለማድረግ ከጸጥታ መዋቅሩ ጋር በቅንጅት እየተሠራ ስለመኾኑም አቶ ደስታው አንስተዋል። በእንጅባራ ከተማ አሥተዳደር የባሁንክ 1ኛ እና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተፈታኝ ተማሪዎችም በመምህራን እገዛ እና በራሳቸው ጥረት በቂ ቅድመ ዝግጅት አድርገው ለፈተና መቀመጣቸውን ተናግረዋል።

በፈተና ሂደቱ 696 ፈታኝ መምህራን፣ ሱፐርቫይዘሮች፣ የፈተና ጣቢያ ኀላፊዎች እና የፀጥታ አካላት ተሳታፊ መኾናቸውንም ከመምሪያው የተገኘው መረጃ ያሳያል።

ዘጋቢ፡- ሳሙኤል አማረ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleኢትዮጵያ ባለብዙ ወገን ግንኙነትን ለማስፈን ቁርጠኛ መኾኗን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ ገለጹ፡፡
Next article“የግጭት ምእራፍን በመዝጋት የሕዝቡን የሰላም ፍላጎት እና የመልማት ጥያቄዎች ለመፍታት በቁርጠኝነት መሥራት ይገባል” ድረስ ሳህሉ (ዶ.ር)