
ባሕር ዳር: ሰኔ 02/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ኢትዮጵያ እና ፊንላንድ የ5 ሚሊየን ዩሮ (313 ሚሊየን ብር) የድጋፍ ስምምነት መፈራረማቸውን የገንዘብ ሚኒስቴር መረጃ አመላክቷል፡፡ የድጋፍ ስምምነቱን የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ ሰመሪታ ሰዋሰው እና የፊንላንድ የውጭ ንግድና ልማት ሚኒስትር ቪሌ ታቪዮ ተፈራርመዋል፡፡
ከፈረንጆቹ 2025 እስከ 2028 የሚተገበረው የድጋፍ ስምምነቱ ለመምህራን የቴክኒክ ድጋፍ በማቅረብ አካታች የትምህር ጥራትን እውን ለማድረግ እንደሚውል ተገልጿል፡፡ ፕሮጀክቱ የመምህራንን ተወዳዳሪነት በማሳደግ ተግባራዊ ዕውቀት እና ክሕሎትን ማጎልበት እንደሚያስችልም ተገልጿል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!