የሉማሜ ከተማ እና የአዋበል ወረዳ ነዋሪዎች በአካባቢያቸው ሰላም ጉዳይ ላይ እየመከሩ ነው፡፡

18

ባሕር ዳር፡ ሰኔ 03/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የሉማሜ ከተማ እና የአዋበል ወረዳ የማኅበረሰብ ተወካዮች ከፌደራል እና ከአማራ ክልል ከፍተኛ መሪዎች ጋር በሉማሜ ከተማ እየመከሩ ነው። ምክክሩም በወቅታዊ የሰላም፣ የልማት እና የመልካም አሥተዳደር ጉዳዮች ዙሪያ ያተኮረ ነው።

በምክክር መድረኩ በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የገጠር ዘርፍ አሥተባባሪ እና የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ ኀላፊ ድረስ ሳህሉ (ዶ.ር)፣ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የንግድ እና ቱሪዝም ልማት ቋሚ ኮሚቴ ምክትል ሠብሣቢ አስቻለ አላምሬ፣ የምሥራቅ ጎጃም ዞን ዋና አሥተዳዳሪ ኑርልኝ ብርሃኑ፣ የምሥራቅ ጎጃም ዞን ኮማንድ ፖስት ሠብሳቢ እና በምዕራብ እዝ የ403ኛ ኮር አዛዥ ብርጋዴር ጄኔራል አዘዘው መኮንን እንዲሁም የክልል እና የምሥራቅ ጎጃም ዞን ከፍተኛ አመራሮች ተሳትፈዋል።

የምሥራቅ ጎጃም የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን መምሪያ መረጃ እንደሚያሳየው መሪዎቹ ሰሞኑን ከደብረወርቅ፣ ከእናርጅና እናውጋ፣ ከብቸና፣ ከእነማይ፣ ከደጀን ከተማ እና ከደጀን ወረዳ ተወካዮች ጋር በአካባቢው ሰላም ጉዳይ ላይ መምከራቸው ይታወሳል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“የመንግሥት ሠራተኞች አገልግሎት አሰጣጥን በማሻሻል ሕዝባዊ አደራቸውን ሊወጡ ይገባል” ደሳለኝ ጣሰው
Next articleየፈተና ውጤት ማስታወቂያ