የኢትዮጵያ ስታትስቲክስ አገልግሎት አሚኮን ጨምሮ ከስድስት የመገናኛ ብዙኅን ተቋማት ጋር የአየር ሰዓት ግዥ ውል ተፈራረመ።

44

አዲስ አበባ: ሰኔ 03/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የኢትዮጵያ ስታትስቲክስ አገልግሎት በ2016 ዓ.ም ለአምስት ዙር የሚያካሂደውን የሥነ ሕዝብ ጤና ጥናት መረጃዎችን ለኅብረተሰቡ ለማሳወቅ አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽንን ጨምሮ ከስድስት የሚዲያ ተቋማት ጋር የአየር ሰዓት ግዥ ውል ተፈራርሟል።

የኢትዮጵያ ስታትስቲክስ አገልግሎት ዋና ዳሬክተር በከር ሻሌ (ዶ.ር) የአየር ሰዓት ግዢው ያስፈለገበትን ምክንያት አብራርተዋል። የሕዝቡ የጤና ሁኔታ ያለበትን ደረጀ ለማወቅ ስለሚደረጉ እንቅስቃሴዎች ሕዝቡ ግንዛቤ እንዲኖረው እና ለሚደረጉ ጥናቶችም ተባባሪ እንዲኾን ለማድረግ ነው ብለዋል።

መገናኛ ብዙኀን ለማኅበረሰቡ ቅርብ በመኾናቸው፣ መረጃዎችንም ለሕዝብ በፍጥነት ስለሚያደርሱ አመኔታን በመጣል ሥራዎችን ለመሥራት በዝግጅት ላይ መኾናቸውንም ዳሬክተሩ ተናግረዋል። ዶክተር በከር በቀጣይ የሚደረገው የሥነ ሕዝብ የጤና ጥናት ስኬታማ እንዲኾን ሁሉም ትብብር ሊያደርግ ይገባል ብለዋል።

ዘጋቢ:- ራሔል ደምሰው

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየሽግግር ፍትሕ ፖሊሲውን መተግበር የሚያስችል ፍኖተ ካርታ ተጠናቅቆ ለውይይት ዝግጁ መኾኑ ተገለጸ።
Next articleበሰላም እና በአብሮነት የመኖር ባሕልን ለማስቀጠል ሕዝቡ በጋራ መሥራት እንዳለበት ተገለጸ።