
ባሕር ዳር: ሰኔ 03/2016 ዓ.ም (አሚኮ)
ሀገራዊ ምክክር ለኢትዮጵያ አዲስ ልምምድ እንደመሆኑ መጠን ጽንሰ ሀሳቡ ከሌሎች የሰላም ግንባታ ወይም ከግጭት አፈታት ዘዴዎች ጋር እየተቀላቀለ ብዥታን ሲፈጥር ይስተዋላል፡፡
የሚከተሉት ነጥቦች ስለ ምክክር ጽንሰ ሀሳብ መሰረታዊ ባህሪያት በአጭሩ ያስረዳሉ፡፡
👉 ምክክር እንደ ድርድር ዜጎች ሊያሳኩ በሚያስቧቸው ውስን የኾኑ ፍላጎቶች ላይ ስምምነቶች እንዲፈጠሩ ከማድረግ ይልቅ ዜጎች ሰብዓዊ፣ ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ችግሮቻቸውን በዘላቂነት የሚፈቱበትን መደላድል ይፈጥራል፤
👉 ድርድር የሚታዩ ወይም የማይታዩ ይዞታዎችን በማከፋፈል ወይም ለአንደኛው ወገን በመስጠት ግጭትን ለማብረድ የሚያገለግል ሲሆን ምክክር ደግሞ በሰዎች መካከል አዲስ የመከባበር፣ የመተማመን እና የመተባበርን ባሕል በማዳበር የዜጎችን ግንኙነት ከፍ ያደርጋል፤
👉 በክርክር ውስጥ የሚዘወተረው አንዱ የሌላውን ሀሳብ ውድቅ በማድረግ የበላይነትን ለማሳየት ሲኾን በምክክር ሂደት ውስጥ ግን ይህ ሁኔታ ፈጽሞ አይኖረም፡፡
በምክክር ሂደት የሚሳተፉ ተሳታፊዎቸ አንዳቸው የሌላኛውን ሀሳብ በአግባቡ በማድመጥ የዚያን ሰው ሀሳብ እና ፍላጎት ለመረዳት ጥረት ያደርጋሉ፤ በሂደቱም የጋራ የሚሉትን እና የሚያግቧቧቸውን መፍትሔዎች ያመነጫሉ፡፡
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!