
ባሕር ዳር: ሰኔ 02/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በሰሜን ወሎ ዞን የአላማጣ ከተማ ነዋሪዎች በሕወሓት በራያ ሕዝብ ላይ እየተፈጸመ ያለውን ግፍ በሕዝባዊ ሰልፍ ገልጸዋል።
ኢ- ሰብዓዊ ድርጊት በግፍ እየተፈጸመበት ያለው የራያ ሕዝብ ቁጣውን በአደባባይ ዛሬ ሰኔ 02/2016 ዓ.ም በሰሜን ወሎ ዞን አላማጣ ከተማ እየገለፀ ይገኛል።
ሕዝቡ የተለያዩ መፈክሮች በመያዝ እየደረሰበት ያለውን በማንነት ላይ የተመሰረተ ጭቆና አውግዟል።
👉ዛሬም ከአሸባሪነት ያልተለየው ወራሪውና አሸባሪው ትህነግ ሕጋዊ የፖለቲካ ፓርቲ ኾኖ እንዲመዘገብ የሚደረገውን ሂደት አጥብቀን እንቃወማለን
👉የራያ ሕዝብ የማንነት ጥያቄ በሀገር አፍራሾች አይቀለበስም
👉እኛ ራያዎች አማራዎች ነን
👉የፌደራል መንግሥት ለራያ ሕዝብ አስቸኳይ ምላሽ ይስጥ
👉የፌደራል መንግሥት ሕግ ያስከብርልን
👉 የፕሪቶሪያው ስምምነት በአስቸኳይ እንዲፈጸም እንጠይቃለን ብለዋል።
ተጨማሪ መረጃ በቀጣይ ተከታትለን የምናደርስ ይኾናል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!