“ጥበባት መጪውን ትውልድ ቅርጽ በማስያዝ እና የከተማችንን የቱሪዝም መስሕብ በማላቅ ከፍ ያለ ሚና ይጫወታሉ” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር)

31

ባሕር ዳር: ሰኔ 01/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) በያሬድ ሙዚቃ ትምህርት ቤት በአሸናፊ ከበደ የክዋኔ ጥበባት ማዕከል የመክፈቻ ሥነ ሥርዓት በመታደሜ ደስ ብሎኛል ብለዋል። አሸናፊ ከበደ ከያኒ ብቻ ሳይሆን የያሬድ ሙዚቃ ትምህርት ቤት የመጀመሪያው ዳይሬክተር ነበር ብለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ.ር) የአዲሱ ማዕከል ዳይሬክተር ግርማ ይፍራሸዋ ደግሞ በቀደመው እና በአሁኑ የኢትዮጵያ ሙዚቃ መካከል ድልድይ በመሆን ያገለግላል ነው ያሉት። ይህን መሰል ድልድይነት እና ቀጣይነት በሁሉም ተቋሞቻችን አስፈላጊ ነው ብለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ ባጋሩት መልእክት እንደገለጹት
ሙዚቃ ኃይል አለው፤ ይህን ኃይል ለወጣቶቻችን አብርሆት ልንጠቀምበት ይገባል።

“ጥበባት መጪውን ትውልድ ቅርጽ በማስያዝ እና የከተማችንን የቱሪዝም መስሕብ በማላቅ ከፍ ያለ ሚና ይጫወታሉ። ይህን ዐቅም በምሉዕነት መጠቀም ይገባናል።” ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር)።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleርእሰ መሥተዳደር አረጋ ከበደ በመዲናዋ የተገነቡ የልማት ሥራዎችን ጎበኙ።
Next articleሳምንቱ በታሪክ