
ባሕር ዳር: ሰኔ 01/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳደር አረጋ ከበደ እና የግብርና ሚኒስትር ግርማ አመንቴ (ዶ.ር) በአዲስ አበባ የተገነቡ የልማት ሥራዎችን ጎብኝተዋል፡፡
በጉብኝታቸውም የለሚ ኩራ የግብርና ምርት መሸጫ ማእከል፣ የእንስሳት ልማት እና ልህቀት ማእከል፣ ለነገዋ የሴቶች ተሃድሶና ማበልጸጊያ ማእከል እንዲሁም ሌሎች የልማት ሥራዎችን ተመልክተዋል፡፡
በአዲስ አበባ የተከናወኑ የልማት ሥራዎች እና ታላላቅ ፕሮጀክቶች የኅብረተሰቡን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡና ለሌሎች ክልሎችም ተሞክሮ መኾናቸውን ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ተናግረዋል፡፡
በተለያዩ ክፍለ ከተሞች የተገነቡት የልማት ሥራዎች ዝቅተኛ የኅብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ የሚያደርጉና የኑሮ ውድነቱን የሚያቃልሉ እንደኾኑ መግለጻቸውን ከከንቲባ ጽሕፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!