
ባሕር ዳር፡ ሰኔ 01/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ለሕዝባዊ ውይይት ወደ ኦሮሚያ ክልል ጅማ ከተማ ያቀኑት በብልጽግና ፓርቲ የአማራ ክልል ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ይርጋ ሲሳይ በማኅበራዊ ትሥሥር ገጻቸው መልእክት አስተላልፈዋል።
ሙሉ መልእክታቸው ቀጥሎ ቀርቧል፦
ብልጽግና ፈርጀ ብዙ ትርጓሜን ያዘለና የኢኮኖሚ፣ ፖለቲካ እና ማኅበራዊ ገጽታ ያለው ነው፡፡ የኢኮኖሚ ብልጽግና፣ የሕዝቦች መሠረታዊ ፍላጎቶች በተገቢና በዘላቂነት ለማሟላት የሚያስችል ፈጣን እና ሁለንተናዊ ዕድገትን በማስመዝገብ፣ ዓለም አቀፋዊ ተወዳዳሪ የሆነ ኢኮኖሚ በመገንባት ፍትሃዊ ተጠቃሚነትን ማረጋገጥና የሕዝቦችን ድህነትና ኋላ ቀርነትን ለመቅረፍ መቻልንም ያካትታል፡፡
ፓርቲያችን ብልፅግና የኢኮኖሚ ፕሮግራሙን እውን ለማድረግ ከሕዝብ ጋር እየመከረ በንቅናቄ መልኩ የፈጸማቸውና ለውጥ ያመጡ ተግባራት ባለቤትም እየሆነ ነው፡፡
በመሆኑም በብዙ የሀገራችን ከተሞች “ከተረጂነት ወደ ምርታማነት ለተሟላ ሉዓላዊ ሀገርነት” በሚል መሪ ሀሳብ ሕዝባዊ ውይይት እየተካሄደ ሲሆን እኔና የሥራ ባልደረቦቼ ለዚህ ሕዝባዊ ውይይት የፍቅርና የልማት ከተማ የሆነችው ጅማ ከተማ ስንደርስ እጅግ በደመቀ መልኩ አቀባበል አድርገውልናል፡፡
ለተደረግልን ደማቅ አቀባበልም የጅማ ከተማን ሕዝብ፣ ለጅማ ከተማ እና ጅማ ዞን አመራሮች ልባዊ ምሥጋና ለማቅረብ እወዳለሁ፡፡
አቶ ይርጋ ሲሳይ
በብልጽግና ፓርቲ የአማራ ክልል ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!