875 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ።

29

ባሕር ዳር: ሰኔ 01/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በሳዑዲ ዓረቢያ በችግር ውስጥ የነበሩ 875 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል፡፡

የዛሬ ተመላሾች ሁሉም ወንዶች ናቸው፤ ከእነዚህ ውስጥም ዕድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች የኾኑ 18 ታዳጊዎች እንደሚገኙ ተገልጿል፡፡

ለተመላሽ ዜጎች ተገቢውን ድጋፍና እንክብካቤ በማድረግ ከቤተሰብ ጋር የመቀላቀል ሥራ እየተሠራ እንደሚገኝም የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።

ከሚያዚያ 4 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ እየተከናወነ በሚገኘው ዜጎችን ወደ ሀገር የመመለስ ሥራ እስካሁን ከ39 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያን መመለሳቸው ተጠቁሟል፡፡

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“አስከፊ ከኾነው የተመፅዋችነት እሳቤ የምንወጣበት ነባራዊ ሁኔታን ለመፍጠር እየተሠራ ነው” የአማራ ክልል ምክትል ርእሰ መሥተዳድር አብዱ ሁሴን
Next articleበብልጽግና ፓርቲ የአማራ ክልል ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ይርጋ ሲሳይ የፍቅርና የልማት ከተማ በሆነችው ጅማ ከተማ ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው።