ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች በሰሜን ሸዋ ዞን አንጎለላ እና ጠራ ወረዳ በመገኘት የአምራች ፋብሪካዎችን የሥራ እንቅስቃሴ ተመለከቱ፡፡

99

ደብረ ብርሃን: ሰኔ 01/2016 ዓ.ም (አሚኮ)ከሰሞኑ የፌዴራል ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ጉብኝት እያደረጉ ነው፡፡
ክልሉ ባለፉት ወራት ያከናወናቸውን የልማት ሥራዎች በጉብኝታቸው ተመልክተዋል፡፡

የሥራ ኀላፊዎቹ ዛሬ በሰሜን ሸዋ ዞን የተሻለ የኢንቨስትመንት ፍሰት ባለበት አንጎለላ እና ጠራ ወረዳ በመገኘት አምራች ፋብሪካዎችን ተመልክተዋል፡፡
ወረዳው ከሰሜን ሸዋ ዞን ከተማ ደብረ ብርሃን በቅርብ ርቀት ላይ የሚገኝ እና ከተማዋን ከአዲስ አበባ የሚያገናኘው ዋናው አስፓልት ነክቷት የሚያልፍ መኾኑ፤ እንዲሁም ባለው አመቺነት ሳቢያ በርካታ አምራች ኢንደስትሪዎች በመቋቋም ላይ ናቸው፡፡

በዛሬው ጉብኝትም በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የከተማ ልማት ዘርፍ አስተባባሪ እና የአማራ ክልል ከተማ እና መሠረተ ልማት ቢሮ ኀላፊ አሕመዲን ሙሐመድ (ዶ.ር)፣ የኦሮሚያ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት የፖለቲካ ዘርፍ ኀላፊ ቢቂላ ሁሪሳ (ዶ.ር) ጨምሮ ከፍተኛ የክልሉ እና የፌዴራል የሥራ ኀላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

ከተመለከቷቸው ፋብሪካዎች መካከል ማሞ ካቻ የወተት ማቀነባበሪያ ፋብሪካ አንዱ ሲኾን እያንዳንዳቸው በቀን ከ35 ሊትር በላይ ወተት መስጠት የሚችሉ 120 ላሞች አሉት፡፡
ፋብሪካው በቀን ከ8 ሺህ ሊትር በላይ ወተት በማምረት እሴት ጨምሮ ለገበያ ያቀርባል፡፡

ዘጋቢ:- ደጀኔ በቀለ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“ወንድም ከወንድሙ ጋር መገዳደል ይበቃናል፣ ልማት ለማምጣት መገዳደልን ማቆም ፍቅርን ማጎልበት አለብን” የባሕር ዳር ከተማ ነዋሪዎች
Next article“የሰላም እጦቱ ከዚህ በላይ እድሜ እንዳያገኝ ማድረግ አለብን” ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ጎሹ እንዳላማው